Friday, June 8, 2012

አሕባሽ ማንነው? ምንድነው? (አጠቃላይ ዳሰሳ)


   አህባሽ የሚባለው አንጃ ከውጪ ሲታይ የሚከተሉት ገጽታዎች አሉት፡፡
1.      “አህባሽ” የኢትዮጵያ ተወላጅ በነበሩት ሼኽ አብዱላሂ ሙሐመድ ዩሱፍ (ወይም ሼኽ አብዱላህ አል-ሐረሪ አል-ሐበሺ) ጠንሳሽነት በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ውስጥ በ1983 ዓ.ል. የተመሰረተ ፖለቲካና ሀይማኖትን አንድ ላይ አጣምሮ የሚራመድ አንጃ (ጀመዓ) ነው፡፡
2.     አንጃው በአረብኛ አጠራር “ጀምዒያቱል መሻሪዒል ኼይሪያቱል ኢስላሚያ” ይባላል፡፡ የእንግሊዝኛ ስሙ “Association of Islamic Charitable Projects” የሚል ነው፡፡
3.     “አህባሽ” የአንጃው ተከታዮች በጋራ የሚጠሩበት የቡድን ስማቸው ነው፡፡ እያንዳንዱ የጀመዓው አባል “ሀበሺይ” ይባላል (ሴት ከሆነች “ሀበሺያ” ትባላለች)፡፡ በሀገራችን ውስጥ ያሉት የአንጃው ተከታዮች ግን “አህባሽ” ከሚለው ስም ይልቅ “የሼኽ ጀመዓ ነኝ” ማለትን ይመርጣሉ፡፡
4.     “አህባሽ” የሚለው ቃል ምንጩ “ሐበሻ” የሚለው የሀገራችን የዐረብኛ ስም ነው፡፡ ይህም የአንጃው መስራች የተወለዱበትን ሀገር (ኢትዮጵያን) ያመለክታል፡፡ የጀመኣው አባላት ይህንን ስም ይወዱታል እንጂ አይቃወሙትም፡፡ ስለዚህ እኛ የአህባሽ ተቃዋሚዎች ያወጣንላቸው ስም አድርጋችሁ እንዳታዩት ያስፈልጋል፡፡ (እውነቱን ለማወቅ አህባሾችን ራሳቸውን ጠይቋቸው፡፡ ዌብሳይቶቻቸውንና የፌስቡክ ቡድኖቻቸውን የሚጠሩበትንም ስም ተመልከቱ)፡፡
5.     አንጃው በሄደበት ሀገር ሁሉ “መንግስታዊ ያልሆነ ማህበር” ተብሎ ነው የተመዘገበው፡፡ በመሆኑም ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ አንዳንድ ተቋማትን (እንደ መድረሳና የጤና ክሊኒክ የመሳሰሉትን) ከፍቷል፡፡ በሀገራችን ውስጥ ግን እንዲህ አይነት ፕሮጀክቶችን የሰራ አይመስለኝም፡፡
6.     አህባሽን የመሰረቱት “ሼይኽ አብዱላህ አል-ሀረሪ” ከሶስት አመታት በፊት ቢሞቱም እስካሁን ድረስ የአንጃው ከፍተኛ መንፈሳዊ መሪ ተደርገው ይታያሉ፡፡ በመሆኑም የጀመዓው አባላት “ሼይኹና” ወይም “ሰይዱና” ይሏቸዋል፡፡ በቤታቸው ግድግዳና በሌሎችም ቦታዎች (በሞባይል ስልካቸውም ጭምር) የመሪያቸውን ፎቶ ያስቀምጣሉ፡፡
7.     የአንጃው ዋና ማዕከል (Head Quarter) ያለው በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ውስጥ ነው፡፡ በተጨማሪም በሶሪያ፣ ዮርዳኖስ፣ ግብጽ፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ካናዳ፣ ጀርመን፣ ዴንማርክ፣ አውስትራሊያ ወዘተ… ቅርንጫፎች አሉት፡፡
8.     አህባሽ በርካታ ተከታዮች ያሉትም እዚያው በሊባኖስ ሀገር ሲሆን በአሜሪካ፣ ካናዳና አውስትራሊያም ጠንካራ ጀመዓ እንደመሰረተ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ወደ ሀገራችን ከገባ ከአስር ዓመታት በላይ ቢሆነውም ብዙ ተከታዮችን መመልመል አልቻለም፡፡ አብዛኛው ህዝብ አንጃው እዚህ መኖሩን እንኳ ያወቀው በቅርቡ ነው፡፡ 
9.     አንጃው የሻፊዒይ መዝሀብ ተከታይ ነኝ ይላል፡፡ የዓቂዳ ትምህርቱም “አሽዐሪ” (ኢማም አቡል ሐሰን አል-አሽዐሪ ያስተማሩት መንገድ) እንደሆነ ያወሳል፡፡ የ“ሪፋዒያ” የሱፊ ጠሪቃ ተከታይ እንደሆነም ይገልጻል፡፡
10.    አንጃው ስብከቱን ለተከታዮቹ የሚያስተምርበት “መርከዝ” (ማእከል) አለው፡፡ በየመርከዙ የሚቀመጡ ሼይኾችንም በቤይሩት እያሰለጠነ በዓለም ዙሪያ ያሰራጫል፡፡ በመርከዙ ተምረው የሚወጡ ጎበዝ ተማሪዎችም ቤይሩት ሄደው የሚማሩበት የከፍተኛ ትምህርት እድል (scholarship) ይሰጣቸዋል፡፡
11.     የአንጃው መንፈሳዊ ትምህርቶች በአብዛኛው የሚያተኩሩት በአቂዳ፤ፊቅህእናተሰውፍ” (Sufism) ላይ ነው፡፡ የትምህርት ቋንቋውም ዐረብኛ ነው፡፡
12.    አንጃው ተከታዮቹን ከሚያስተምርባቸው የመማሪያ መጽሀፍት መካከል በስፋት የሚታወቁት ሁለት ናቸው፡፡
12.1      ሙኽተሰር አብዱላህ አል-ሀረሪ
a)   ይህ ጀማሪዎች የሚማሩበት መጽሀፍ ሲሆን የአቂዳ፤ ፊቅህ፤ ከላም (speculative theology) ትምህርቶችን አካቷል፡፡
b)  መጽሀፉ የዛሬ 100 አመት ገደማ በአንድ የመናዊ ሼኽ እንደተጻፈ በመግቢያው ላይ ተጠቅሷል፡፡ሼኽ አብዱላህ የጻፉት ሸርሁን (ማብራሪያውን) ነውተብሎም ተጽፎበታል፡፡ ነገር ግን ከመጽሀፉ 70% በላይ የሚሆነው ክፍል የተያዘው ሸርሁነው፡፡
c)   መጽሀፉ በእንግሊዝኛና በአማርኛ ተተርጉሟል፡፡ የእንግሊዝኛው ትርጉም ቀለል ባለ አቀራረብ የተዘጋጀ ሲሆን አማርኛው ግን ልክ እንደ አረብኛውየመጽሀፉ አዘጋጅ እንደዚህ አሉ!” እያለ ነው ትምህርቱን የሚዘረዝረው፡፡ (የአረብኛው መጽሀፍቃለል ሙአሊፉእያለ የሚሄድ የትረካ አቀራረብ አለው)፡፡
d)  የመጽሀፉ ዋና ክፍል (“ሸርህያልሆነው) ላይ ላዩን ሲታይ እስላማዊ መንገድን የተከተለ ይመስላል፡፡ ነገር ግን በእስልምና ውስጥ የማይታወቁ አስገራሚ አቋሞች ይበዙበታል፡፡ ይህንን በትክክል የምትረዱትም ከዋናው ምንባብ ሳይሆንሸርህተብለው ከቀረቡት አደገኛ ትንተናዎች ነው፡፡
e)   ከሁሉም በላይ ደግሞይህንን ያላለ ይከፍራልበዚህ ያላመነ ከኢስላም ወጥቷል”፤ “ይህንን ያደረገ ካፊር ነውየሚሉ አስፈሪ አባባሎች ስለሚበዙበት በትእግስት አንብቦ መጨረሱ ራሱ ከባድ ነው፡፡
12.2    ሁለተኛው መጽሀፍ ቡግየቱ- ጣሊብ ተብሎ ይጠራል፡፡
a)     በዚህኛው መጽሀፍ የሚማሩት በትምህርት ከፍ ያሉ ተማሪዎች ናቸው፡፡ (ይህኛው መጽሀፍ በእንግሊዝኛና በአማርኛ ቋንቋዎች ስለመተርጎሙ አላውቅም)፡፡
b)    ቡግየቱ-ጣሊብ በስፋት ካልሆነ በስተቀር በይዘቱ ከሙኽተሰር ጋር አንድ ነው፡፡ ቢሆንም በሙኽተሰር ውስጥ የሌሉ በርካታ አስገራሚ ፈትዋዎች አሉበት፡፡
13.    አህባሽ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚያሳትመው መጽሄትመናረል ሁዳይባላል፡፡ በቤይሩት ከተማሰውቱል ኒዳየሚባል ሬድዩ ጣቢያ አለው፡፡ በአለም ዙሪያ በርካታ የኢንተርኔት መረቦችንም ዘርግቷል፡፡ ከነዚህም መካከል www.aicp.org ዋነኛው ድረ-ገጽ ዌብሳይት ነው፡፡
14.    ይህ አንጃ
14.1     በአፈጣጠሩ፣ በእድገቱ፣ በእምነት ፍልስፍናውና በድርጊቶቹ በጣም ግራ የሚያጋባና አነጋጋሪ (controversial) የሆነ ነው፡፡
14.2    በጅምሩ ላይ ከሶሪያ ጋር ይቀራረብ ስለነበር በሶሪያ ተጽእኖ የሚመራ ይመስል ነበር፡፡ እስካሁን ድረስም ከሶሪያ መንግስት ጋር መልካም ግንኙነት አለው፡፡ ሌሎች ድርጊቶቹን ስናይ ግን አህባሽና ሶሪያ የጥቅም ግንኙት እንጂ የፍቅር ግንኙነት የላቸውም ማለታችን አይቀርም፡፡ 
14.3    መላው የሊባኖስ ህዝብ በሹክሹታ እንደሚያወራውና በኢንተርኔት እንደሚጻፈው ከሆነ አህባሽ የእስራኤል የስለላ ቡድን (ሞሳድ) በረቀቀ ዘዴ የሚያሽከረክረው ድርጅት ነው፡፡ በመሆኑም በሊባኖስ ውስጥ ጸረ-እስራኤል አቋም ያላቸውን ማህበራትና የፖለቲካ ቡድኖች በሙሉጠብ አጫሪዎች ናችሁእያለ ይቃወማል፡፡ የፍልስጥኤም የነጻነት ጥያቄን በሚመለከትምበሰላማዊ መንገድ ብቻ ነው መፈጸም ያለበትየሚል ያልተብራራ አንቀጽ በፖለቲካ ማኒፌስቶው ላይ እንዳሰፈረ የዛሬ 15 አመት ገደማ ስለቡድኑ የጻፉት ኒዛር ሀምዛ ይገልጻሉ፡፡
14.4     በቅርቡ እነ ሀጋይ ኤርሊችን የመሳሰሉ ጽዮናዊያን አህባሽ የሚከተለው ለዘብተኛ ኢስላማዊነት ለዓለም አስፈላጊ የሆነ የሰላም መድሀኒት ነው እያሉ መጻፋቸውም ከላይ የተባለውን ጥርጣሬ ወደ እውነታ ከፍ ያደርገዋል፡፡
14.5     ከሁሉም በላይ አህባሽ በአለም ዙሪያ ያሉ ሙስሊሞችን ያስደነገጠው በሶስት አቋሞቹ ነው፡፡
a)     በቅድሚያ ከየት እንደተገኙ የማይታወቁ የእምነት ፍልስፍናዎቹን የማይቀበሉ ሙስሊሞችን በጅምላካፊር ናቸውበማለት ይፈርጃል፡፡
b)    በሁለተኛ ደረጃም ከምዕራባዊያን ጋር ቅጥ ያጣ የወዳጅነት ትስስር አለው፡፡ ሙስሊሙን እንደጠላት ለሚያዩት ምዕራባዊያን አህባሽ ውድ ልጃቸው ነው፡፡ በተለይ ከሴፕቴምበር 11/2001 ወዲህ ተፈላጊነቱ ጨምሯል፡፡
c)     በሶስተኛ ደረጃም ሙስሊሞችን ለጥቃት  የሚያሳድድሙስሊም ነኝባይ አንጃ መሆኑ በጣም እያነጋገረ ነው፡፡ አንጃው በይፋ ሲናገርጠላቶቼ ወሀቢዎች ናቸውይላል፡፡ ይህ ግን የአንጃው የማስመሰያና የመከፋፈያ ስልት መሆኑን ቡድኑን በቅርበት የሚያውቁ ምሁራን ይገልጻሉ፡፡ጠላቶቹ መላው ሙስሊሞች ናቸውበማለትም ያስረዳሉ፡፡
አህባሽ በጥቅሉ ሲታይ ይህንን ይመስላል፡፡

No comments:

Post a Comment