ኡባህ አብዱሰላም ሰዒድ
አህባሽ የተባለው አንጃ በቤይሩት ከተማ ሲመሰረት የእድር አይነት መልክ ነበረው፡፡ ከጥቂት አመታት በኋላ ግን ጠንከር ያለ ማህበራዊና ሀይማኖታዊ ቡድን ሆኖ ብቅ አለ፡፡ ለዚህ የረዳው ቡድኑ በረጅሙ የሊባኖስ የርስ በርስ ጦርነት ወቅት ንቁ ተሳትፎ ያልነበረው መሆኑና ይልቁንም የሊባኖስ ህዝብ እንደ ነጻ አውጪ በሚመለከተው የሶሪያ የጦር ሀይል መታገዙ ነው፡፡ የሚገርመው ነገር ቡድኑ በሶሪያም እየተደገፈ ከእስራኤልና ከምእራባዊንም ጋር አስገራሚ ቁማሮችን የሚጫወት መሆኑ፡፡
የአህባሽ መርዘኛነት እዚህ ላይ ነው! “ሶሪያን እኛ የምናውቃት የምእራባዊያን ጠላት ናት” በሚል ነው፡፡ ይህንን የሚያስብ ሰው “አህባሽ ከጽዮናዊያን ጋር የጠነከረ ወዳጅነት ይመስርታል” ብሎ አይጠረጥረም፡፡ ግን አድርጎታል!! ትንሽ ጥቅም የሚያገኝ ከሆነ ከማንም ጋር አደገኛ ቁማሮችን ይጫወታል፡፡ ቡድኑ ነጋ ጠባ የሚወርፈውን “ወሀቢያ” የሚባል ቡድን “አብረን እንታገለው” የሚለውን ሰው ካገኘማ ደስታውን አይችለውም፡፡ አንድ የሚያሳዝነኝ ነገር ቢኖር “አህባሽ” የሚቀርባቸው ቡድኖችና መንግስታት ሁሉ “ጸረ-ኢስላም” መሆናቸው ነው፡፡ የሶሪያዎቹ የ“አለዊ” እምነት ተከታዮች፤ የአይሁድ ጽዮናዊያን፤ የአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም፤ የቱርክ ወታደራዊ መኮንኖች ወዘተ… ሁሉም ጸረ-ሙስሊም ናቸው፡፡
አህባሽ “የሙስሊሙን ዓለም እንዴት ጸጥ እናድርገው?” እያሉ ሲጨነቁ ለነበሩት ምዕራባዊያን ተመችቷል፡፡ በተለይ ከሴምቴምበር 11/2001 ወዲህ ተፈላጊነቱ በጣም ጨምሯል፡፡ ለዓለም ሙስሊሞችስ ምን አስገኝቷል? በዚህ በኩል አንጃው ምንም የቀናው ነገር የለም፡፡ የታሪክ መዝገቡ በአሳፋሪ ፋይሎች የታጨቀ ነው፡፡ ከፊሊፒንስ እስከ ካናዳ፤ ከፊንላንድ እስከ ደቡብ አፍሪካ ያሉት ሙስሊሞች በሙሉ “አህባሽ” የጥመት እና የኑፋቄ ቡድን መሆኑን በይፋ አውጀዋል፡፡ በርካታ ምሁራን፤ እስላማዊ ተቋማትና ቡድኖች አህባሽን ያወገዙባቸውን ልዩልዩ ፈትዋዎች ሰጥተዋል፡፡ ከነዚህ መካከልም አንዳንዶቹ እንደሚከለተው ቀርበዋል፡፡
1.
አለም አቀፍ የፈትዋ አስተዳደርና የምርምር ተቋም (በማሌዥያ የሚገኝ) በአህባሽ ጥመትና ኑፋቄ ላይ የተላለፉ በርካታ ፈትዋዎችን መዝግቧል፡፡ ከነርሱ መካከል አንዱን በሚከተለው የኢንተርኔት አድራሻ ማየት ትችላላችሁ፡፡
2.
የግብጽ ሙፍቲ ዶ/ር ዓሊ ጁምዓ
የአህባሽን መርዘኛነት ያወገዙበትን ፈትዋ ከሚከተለው አድራሻ ማየት ትችላላችሁ፡፡
3.
አህባሾች “የሱፊያ” እና “የሱፊዎች” ጠበቃ እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡ ትክክለኛው “ተሰዉፍ” (Sufism) ከነርሱ ዘንድ እንዳለም ያወራሉ፡፡ የሱፊ ቡድኖች ግን አህባሽ ጠማማ አንጃ መሆኑን በይፋ ሲያሳውቁ ነበር፡ ለምሳሌ ያህልም የአለም ትልቁ የሱፊዎች ማእከል መሆኑ የሚነገርለት የነቅሽባንዲያ ቡድን በአህባሽ ጥመትና ኑፋቄ ላይ ያሳለፋቸውን ልዩ ልዩ ፈትዋዎች ከሚከተለው ዌብ ሳይት ላይ ማንበብ ይቻላል፡፡
4.
የሰሜን አሜሪካ የሱኒ (አህሉ ሱንና ወልጀመዓ) ሙስሊሞች ማህበር የአህባሽን ጥመት አስመልክቶ ያስተላለፈው ፈትዋ ከማህበሩ ድረ-ገጽ ይገኛል፡፡
5.
ይህንኑ የአሜሪካ ሙስሊሞች ማህበር ከሚመሩት ምሁራን አንዱ የሆኑት ዶ/ር ጂብሪል ፉአድ ሀዳድ ለልዩልዩ ጥያቄዎች መልስ በሚሰጡበት ዌብ ሳይት ላይ አንድ ሰው “ወደ አህባሾች መርከዝ ሄጄ ትምህርታቸውን መከታተል ይፈቀድልኛል?” ብሎ ሲጠይቃቸው “ከነዚህ የውሸት ሱኒዮች (Pseudo-Sunni) አንድም አይነት ትምህርት መቀበል አይፈቀድም” በማለት መልሰዋል፡፡ ሙሉውን ጥያቄና መልስ ከሚከተለው አድራሻ ማየት ትችላላችሁ፡፡
6.
እኚሁ እስላማዊ ምሁር በአህባሽ ላይ የሰጧቸውን ልዩ ልዩ ፈትዋዎች ለማንበብ የሚከተለውን የዌብሳይት አድራሻ ክፈቱ፡፡
7.
አህባሾች የፊቂህ መዝሀባቸው “ሻፊዒይ” እንደሆነ ደጋግመው ያወራሉ፡፡ አቂዳን የሚያስተምሩት በኢማም አቡል ሀሰን አል-አሽዐሪ መንገድ እንደሆነም ይጽፋሉ፡፡ በአለም ዙሪያ ያሉትና የሻፊዒን መዝሀብና የአሽዓሪን የአቂዳ ትምህርት የሚቀበሉ ሙስሊሞች ግን አህባሽ የጥመትና የኑፋቄ ቡድን እንደሆነ በአንድ ድምጽ ይናገራሉ፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ስለ አህባሽ ያደረጉትን የኢንተርኔት ውይይት ከሚከተሉት ሁለት ዌብሳይቶች ማየት ትችላላችሁ፡፡
a.) http://www.sunniforum.com/forum/showthread.php?2953-ANSWERED-Who-are-the-habashis-%28al-ahbash%29
8.
አህባሾች ከሺዓ ቡድኖች ጋር እንደማይስማሙ ከዚህ ቀደም ተናግሬ ነበር፡፡ ማስረጃ ከፈለጋችሁ አህባሽ በዓለም ዙሪያ ከታወቀውና “ሂዝቡላህ” ከተሰኘው የሺአ ቡድን ጋር ባለፈው አመት በቤይሩት ጎዳና ላይ ያደረጉትን ውጊያ ከሚከተለው ድረ-ገጽ ተመልከቱ፡፡
የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን እንዲመራ የተመረጠው ቡድን የኋላ ታሪኩ ይህንን ይመስላል፡፡ እኛም የምንፋለመው የአለም ሙስሊሞች በጥመትና በኑፋቄ ካወገዙት ከእንደዚህ አይነቱ ቡድን ጋር ነው፡፡ ቡድኑ ለዲናችን ጠንቀኛ መሆኑ በአንድ ቃል የተመሰከረ ሀቀኛ ነገር ስለሆነ በዚህ ላይ ጥርጣሬ አይግባችሁ፡፡ የጀመርነውን ፍትሃዊ ትግል በሰላማዊና ህጋዊ መንገዶች ሁሉ እንቀጥልበታለን፡፡
ድል የኢስላም ነው! አላሁ አክበር!
No comments:
Post a Comment