በዑመር
ረመዳን
የሰው ልጅ በመልክና በቁመና እንደሚለያየው ሁሉ በአመለካከትም ይለያያል፡፡ አብዛኛውም ሰው የየራሱን አመለካከት
ይዞ መኖርን ይመርጣል፡፡ ነገር ግን ልዩነቱን እንደያዘ ከሌሎች ጋር በአንድነት መኖር ይችላል- የግሉን ለግሉ በማድረግ በጋራ ጉዳዮች ላይ አንድ በመሆን፡፡ በሌላ
አነጋገር “በልዩነት ውስጥ አንድነትን በመፍጠር” ማለት ነው፡፡
አንድነት (ህብረት) ውበት ነው፡፡ አንድነት ጥንካሬ ነው፡፡ አንድነት ሀይል ነው፡፡ ሰዎች በየአካባቢያቸው የሚከሰቱ
ማህበራዊ ችግሮችን ለማስወገድ የሚችሉት አንድ ሁነው ሲንቀሳቀሱ ነው፡፡
“አንድነት” በኢስላም አይን ሲታይ ደግሞ ለጋራ ጥቅማችን የምናደርገው ትስስር ብቻ ሳይሆን ሀይማኖታዊ ግዴታም
ሆኖ ይገኛል፡፡ ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ዓሊም ዶ/ር ጀይላን ኸድር ሚያዚያ 28/2004 ዓ.ል. በአየር ጤና አንሷር መስጂድ ተዘጋጅቶ
በነበረው የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም ላይ በአጽንኦት እንደተናገሩት “በቁርአን፣በሱንና እና በአላህ የአንድነት ገመድ መተሳሰር
በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በዓለም ሙስሊሞች ላይ ግዴታ የተደረገ ኢስላማዊ ደንብ ነው፡፡ ይሄን አስመልክቶ
አላህ (ሱ.ወ.) በቁርዓኑ ሲናገር “ሁላችሁም በአላህ ገመድ ተሳሰሩ፣አትለያዩም” ብሎናል፡፡
አላህ ሱ.ወ. ዋጂብ (ግዴታ) ያደረገብን ኢስላማዊ አንድነት ለህይወታችን በርካታ ጥቅሞች አሉት፡፡ ነብዩ መሀመድ
ሰ.ዐ.ወ. ሙስሊሞች ሊረዳዱና ሊተባበሩ እንደሚገባ በሐዲሳቸው ሲያስተምሩ እንዲህ ይላሉ፤
“አንድ ሙሰሊም ለሌላው ሙስሊም ወንድም ነው፡፡መጥፎ ሊተገብርበትና ለሌላ ወገን አሳልፎ ሊሰጠው አይገባም፡፡
የአንድ ሙስሊምን ጉዳይ ያሟላ፣አላህ የርሱን ጉዳይ ይሞላለታል፡፡ከአንድ ሙስሊም ላይ አንዳች ችግር ያነሳ፣አላህ በፍርዱ ቀን ችግሩን
ያነሳለታል፡፡ አንድን ሙስሊም የጠበቀና የተከላከለ አላህ በፍርዱ ቀን እሱን ይጠብቀዋል፣ይከላከልለታል፡፡ ” (ቡኻሪ ዘግበውታል)
ካለመተባበር ወደ መተባበር
ከጥቂት አመታት በፊት በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ዘንድ ሲታይ የነበረው
መከፋፈልና መቆራቆስ ናላችንን አዙሮት ነበር፡፡ በጥቃቅንና ምክኒያቶች የሚፈጠሩ ሽኩቻዎች ሙስሊሞችን ሆድና ጀርባ እስከማድረግ ደርሰዋል፡፡
የመጅሊስ አመራር ተብለው የተሾሙብን “ሀጂዎች” እና “ሼኮች” ችግሩን ከማስወገድ ይልቅ እንደ እብድ ገላጋይ ዱላ እያቀበሉ ህዝበ
ሙስሊሙን ሲያናቁሩት ነበር፡፡ ዘንድሮ ግን የባሰውን አመጡበን፡፡ “ህገ-መንግስት እናስተምራለን” በሚል ሰበብ ኢማሞችና ሙአዚኖቻችንን
በስልጠና አዳራሾች ውስጥ እያጎሩ “እስከዛሬ የቆያችሁበት እስልምና የተበከለ ነው፡፡ ስለዚህ ሁላችሁም ሸሀዳ በድጋሚ መያዝ አለባችሁ፡፡
ለዚህ ደግሞ ቅድመ ግዴታው “ኢብን ተይሚያህ ካፊር መሆኑን ማወጅ ነው”፤
የሚል ሰበካ ጀመሩ፡፡ ይሄኔ ግን ህዝበ ሙስሊሙ “በቃኝ!” አለ፡፡ “እንዲያውም እስከዛሬ በጫንቃችን ላይ ለጨፈራችሁት በህግ መጠየቅ
አለባችሁ” የሚል ድምጽ አሰማ፡፡ “አሽሻዕቡ ዩሪዱ ኢስቃጠል መጅሊስ!” በሚል መፈክር ዙሪያ ተሰለፈ፡፡
“እሳት ቢያንቀላፋ ገለባ ጎበኘው ነው!” ነገሩ፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ
ለረጅም ጊዜ በራሱ ተቋም ላይ የሚምነሸነሹትን የመጅሊስ አመራሮች አይቶ እንዳላየ ቢያሳልፋቸውም “ዘመቻ ጥምቀተ አሕባሽ”ን (Ahbashism
Campaign) ግን ሊያስተናግድላቸው አልቻለም፡፡ ለወትሮው በየምክንያቱ ሲናቆር የነበረው ሁሉ “ዘመቻ ጥምቀተ አሕባሽ”ን ለማክሸፍ
በአንድነት ተሰልፏል፡፡ ሙስሊሞችን በተበከለ ፍልስፍና ለማጥመቅ የተወጠነውንም “ይሁዲ ሰራሽ” እቅድ አከሸፏል (ያልተቋጩ ጉዳዮች
ቢኖሩም እንኳ)፡፡ የአንድነትን ውጤት በተግባር አሳይቷል፡፡ የህብረት ጥቅምንም በተጨባጭ አስመሰክሯል፡፡ አል-ሓምዱሊላህ!!
የአንድነታችን መሰረቶች
በሙስሊሞች ጉዳይ መጽሄት የሚያዚያ ወር እትም ላይ አቡ ሃቅ የተባሉ
ወንድማችን “ቀጣይ ፈተናዎቻችንና የመፍትሄዎቻችን ቁልፎች ” በሚል ርእስ በጻፉት መጣጥፍ የአንድነትን አስፈላጊነት ሲያትቱ እንዲህ
ብለው ነበር፡፡
“ለምንድነው አንድነት የሚያስፈልገን? የሚል ጥያቄ ሲነሳ ሶስት
ነገሮችን ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡
አንደኛ፡- የአላህ ትዕዛዝ ስለሆነ! ቁርኣን “በአላህ ገመድ አንድ
ሆናችሁ ተያያዙ፣እንዳትለያዩ” ይላል፡፡ ይህን የአንድነት ስሜት አጠናክረን እንድንይዝ አላህ ስለሚያዘን የአላህን ትዕዛዝ መፈጸምም
ጭምር ነው፡፡
ሁለተኛ፡- በአንድ መንግስታዊ መዋቅር ውስጥ የኖርን ሰዎች ተመሳሳይ
የሆኑ ታሪኮችን አሳልፈናል፡፡ ተመሳሳይ የሆኑ ገድሎችን ሰርተናል፡፡ ተመሳሳይ የሆኑ ጭቆናዎችንም አሳልፈናል፡፡ በአሁኑ ጊዜም ተመሳሳይ
በሆነ ፖለቲካዊ ሁኔታ ውስጥ እየኖርን ነው፡፡ ለወደፊትም ተመሳሳይ የሆኑ ባህላዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊና ማህበራዊ ሁኔታዎችን እንጋራለን፡፡
ስለዚህ በጣም የተያያዝንና የተጣመርን ነን፡፡ አንዳችን ላይ የሚደርሰው ችግር በሌላው ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ ቀላል ባለመሆኑ የሚያስተሳስሩን
ገመዶች ጠንካራ ናቸው፡፡ ስለዚህ መብታችን ሲጣስ በጋራ መቆም የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ግዴታ ይሆናል፡፡
ሶስተኛ፡- በአንዳንድ አካባቢዎች አነስተኛ ሆነው የሚኖሩ ሙስሊሞች
አሉ፡፡ ለነዚያ ሙስሊሞችም ድምጻችንን ለማሰማት እንድንችል አንድ መሆናችን ወሳኝነት አለው፡፡ ሁላችንም በአንድነት ተጋግዘን የሚደርስባቸውን
ጭቆና ለማስወገድ ካልጣርን በሌላ ማህበረሰብ ተውጠው በበደልና ጭቆና ውስጥ ይሰነብታሉ ማለት ነው፡፡”
የትግላችን ዋነኛ ውጤት
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ባለፉት አስር ወራት ሲያስተጋቧቸው የነበሩት
“የአህባሽን የተጣመመ አስተምህሮት አንፈልግም ፣ያልመረጥናቸው የመጅሊስ ባለስልጣናት አይወክሉንም” የሚሉ መፈክሮችና እምነትን በነጻነት
የማራመድ መብት ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ ምላሽ ባያገኙም በታሪክ ማህደር ላይ ሊሰፍር የሚገባ አንድ አቢይ ቁም ነገር አስመዝግበዋል፡፡
ይህም አንድነታቸውን ለማጠናከር መቻላቸው ነው፡፡ በዚህም የሙስሊሙን ህብረት እንደ ጦር የሚፈሩ ሀይሎች ካስቀመጡላቸው ወጥመድ ውስጥ
በመግባት ይፈጥሩት ከነበረው ከፍተኛ የመፈረካከስ አደጋ ለማምለጥ ችለዋል!፡፡ በሌላ በኩል አሁን የተፈጠረው ህብረት መጪው የኢትዮጵያ
ሙስሊም ትውልድ (generation) በጤናማ መሰረት ላይ የተገነባ ይሆን ዘንድ የመነሻ ግብአት ሊሆን ይችላል የሚል ተስፋን ያሳድራል፡፡
ለነገም ቢሆን-አንድነት
ዛሬ በኢስላም ላይ የተጋረጠው አደጋ አቀራርቦናል፡፡ “ከአክራሪነት
የጸዳ መንገድ ነው” ተብሎ በአሜሪካ፤ ጽዮናዊያን፤ ፌዴራል ጉዳዮች ወዘተ... የተጨበጨበለት የ“አሕባሽ” ፈተና የማንቂያ ጥሪ ሆኖልን
አንድነታችንን የሙጥኝ ብለናል፡፡ ነገስ? ወደ ድሮው ሽኩቻና ግለኝነት ልንመለስ ነው? “ውሃ ሊቋጥሩ” በማይችሉ ሰበባ ሰበቦች እያተፋጨን
ህብረታችንን ልናበላሸው ነው? አንድነት የሚያስፈልገው በመከራና ጭንቅ ጊዜያት ብቻ ነው?
አይሆንም ያ ጀመዓ! ኢስላም ምን ጊዜም ቢሆን በአንድነት ያዛል፡፡
ዛሬ ተአምራዊ ውጤት ያሳየንበትን ህብረት ነገም ቢሆን መቀጠል አለብን፡፡ የኢስላም ጠላቶችን ፋታ የነሳንበት አንድነታችን ዘላቂ
እንዲሆንልን እስከመጨረሻው መጣር አለብን፡፡
“ዘመቻ ጥምቀተ አሕባሽ” በተሰኘው ክፉ ውጥን ጽዮናዊያን የፈበረኩት
የአሕባሽ ፍልስፍና በኛ ላይ እንዲሞከር የተፈረደብን ሕብረታችንን ባለማጥበቃችን ነው፡፡ አሁን ፈተናውን ለመቋቋም የቻልነው ደግሞ
አንድ በመሆናችን ነው፡፡ ስለዚህ በከባድ ጥረትና መስዋእትነት የገነባነውን ህብረት መንከባከብ አለብን፡፡ ፈጣሪያችን አላህ (ሱ.ወ)
እርዳታውን የሚለግሰን አንድነታችንን ካጠበቅን ብቻ ነውና፡፡ ማን ያውቃል? አላህ (ሱ.ወ) አህባሽ የተባለውን የጥመት ቡድን ወደ ኢትዮጵያ የላከበት ዋነኛ
ምክንያት ኢስላማዊ አንድነት በውስጡ ያዘለውን ከባድ መልእክት ለኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ማስተማር ቢሆንስ?
አላህ ከኛ ጋር ይሁን!... ያ ኢስላማዊ አላህ አንድነታችንን ጠብቅን!... አሚን...
this unity should on tewhid, following the quran and suna. the qureish didnt fight our beloved prophet pbuh for his saying allah is the creator. but they fought with him because he teaches allah is the only worthy of worship. so every step to unity should be on the giude line of quran and suna
ReplyDeletewe shoud be woryy how much of the people of ethiopia knows why we are against ahbash. if the people who are opposing ahabsh are .................it is difficult. we on this occasion should teach others the basic knowledge of islam tewhid
ReplyDeletevictory for islam
ReplyDelete