Wednesday, May 23, 2012

በፊርዶስ ላይ የደረሰዉ ኢ-ሰብአዊ ግፍ

Source :  ድምፃችን ይሰማ 
ኢናሊላሂወኢና ኢለይሂ ራጂኡን
በሴት ሙስሊሞች ላይ የሚደረሰዉ ግፍና መከራ እንደቀጠለ ነዉ:: ይህም የግፍ ዜና ምንጮቻችን እንደዘገቡልን እናቀርበዎል:: ጉዳዩ እንደሚከተለዉ ነዉ በቅርቡ የፌደራል ጉዳዮች ከየክፍለ ከተማዉ የተመረጡ ሰዎችን በመጥራ ስብሰባ አካሂዶ ነበር:: በዚህም ስብሰባ ላይ ከኮልፌ ክ/ከተማ ሶስት ሰዎች የተሳተፍ ሲሆን ሁለት ወንድ እና አንዲት ሴት ይገኙበታል:: በዚህ ስብሰባ ላይ የኮልፌ ክ/ከተማ ነዎሪ የሆነችዉ ፍርዶስ የተባለች እህታችን ትገኝበት ነበር:: በስብሰባዉ ላይ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራዉ ተገኝተዉ ስብሰባዉን አካሂደዉ እንደነበር ምንጮች ገልፀዎል:: በስብሰባዉም ላይ ዶ/ር ሽፈራዉ እጅግ አፀያፊና ድንበር ያለፍ ንግግሮችን በህዝበ ሙስሊሙ በተመረጡት ኮሚቴዎች ላይ በመናገራቸዉ ይህንን የሰዉየዉን ዘለፉና ስም ማጥፉት መሸከም እና መታገስ ያቃታት እህታችን ፍርዶስ ዶ/ር ሽፈራዉ ለተናገረዉ ንግግር እልህ በተሞላበት ቃል ተቃዉሞአን በመግለፅ "ዶ/ር ሽፈራዉ ሴት የሴት ልጅ ነህ" በማለት የስብሰባ አዳራሹን ጥላ ወታለች:: ከአዳራሹ ወታ ወደግል መኪናዎ(የመኪናዎ ስም ቶዬታ ቪትዝ ነዉ) በማምራት ወደ መጣችበት ለመሄድ እንቅስቃሴ ስትጀምር በሁለት ላንድክሩዘር መኪና ደህንነቶች ተከትለዉ ያስቆሟትና አፍነዉ እሷንም መኪናዎንም ይዘዎት የሰወራሉ:: ከዚ ቡሀላ ነበር እህታችን ፍርዶስ ላይ ይህንን ኢ ሰብአዊ ድርጊት የፈፀሙባት:: እህታችን ፍርዶስን ያለምንም እርህራሄ በኤሌክትሪክ ሾክ አቃጠሏት:: ወድያዉኑ እህታችን መናገርም መንቀሳቀስም አቆመች::ይህንን ኢ ሰብአዊ ድርጊት ከፈፀሙባት ቡሀላ መኪናዎን እና እሷን መኗሪያ ቤቷ በር ላይ ጥለዎት ሄዱ::ቤተሰቧ እጅግ በመደናገጥ ልጃቸዉን ለመታደግ ጥረታቸዉን ተያያዙት:: የፍርዶስ አባት የልጁን ሂወት ለመታደግ ለህክምና በፍጥነት ወደ ዉጪ ሀገር (ሳኡዲ አረቢያ) ይዟት ይሄዳል:: ነገር ግን በኤሌክትሪክ ሾክ ከጥቅም ዉጪ ባደረጉዎት ደህንነቶች ምክንያት የአላህ ዉሳኔ ሆነና ፍርዶስ ለህክምና በሄደችበት ይህንን መራራ ስቃይ ተገላግላ ወደ አኼራ ነጎደች:: ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን! 
ይህ ሁላ ግፍ ሳይበቃ ይህንን የፈፀሙትን ግፍ እንዳይሰማባቸዉ ለማድረግ ወላጅ እናቷን አፍነዉ ወስደዉ እስካሁን ድረስ እናቷ የደረሱበት አልታወቀም:: እንደምታስታዉሱት በቅርቡም በአንዲት የጃዕፈር መስጂድ ጀምአ አባል በሆነች እህታችን ላይ ተመሳሳይ አፈና አካሂደዉ አንድም ሰዉነቷን ሳያስቀሩ እራሷን ስታ እስክትወድቅ ድረስ በመደብደብ አዉራ መንገድ ላይ ጥለዎት ሄደዉ እስካሁን አልጋ ላይ እንደሆነች የሚታወስ ነዉ:: ኧረ ያ አላህ መከራችን ይብቃቹ በለን:: በሙስሊሞች ላይ የሚደርሰዉን ግፍና መከራ ላልሰሙት እናሰማ! ሁሌም በዳይ እንደበደለ አይቀርም! የእጁን ያገኛል ኢንሻላህ! ይህንን ጉዳይ እስከመጨረሻዉ በመከታተል የተደረሰበትን እናሳዉቃለን:: እስከዛዉ ይህንን የመንግስት አካላት እየፈፀሙ ያሉትን ግፍና በደል ላልሰሙት በማሰማት እና እህታችንንም አላህ ጀነት እንዲያስገባልን በዱአ እንለምነዉ::

7 comments:

  1. Allah yejenet mushera yadirgat! Esuas shehid honech egna eskemech muslim ehtochachin ena wendmochachin eyetegedelu zim bilen enkemetalen?

    ReplyDelete
  2. Ameen ALLAH ye Jannat yebelat. ande ken yemetal muslim beselam yeminorebet zize INSH'ALLAH kerbe new teleku neger hulgize duaa madereg new ALLAH kegna gar new menem anferam

    ReplyDelete
  3. Amin
    ALLAH SHIDNETAN YQBELAT.

    ReplyDelete
  4. oh............I'm very shocked, ..May Allah reward her in jennat_l ferdos....Aimn

    ReplyDelete
  5. this is a begninig of failing for MELES regime& intial point of our victory,inshallah.for our dear sister firdous inshallah ALLAH'S firdous.

    ReplyDelete